EthioGreen LLC is a registered import / export company located in Washington, DC
202-558-8337
EthioGreen
President Obama Explains Healthcare

President Obama Explains Healthcare.gov
Ethiopian Political Parties
Ethiopian Political Parties
Categories

Ethiopian Television ETV Satellite Frequency
Struggle Over the Nile – Tension and suspicion

የግብፅ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ ኢትዮጵያን በቅርቡ እንደሚጎበኙና አዲስ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንደሚመሠርቱ በግብፅ ለኢትዮጵያ አምባሳደር መሐመድ ድሪር ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የሚጎበኙት በተለይ በዓባይ ጉዳይ ለመደራደር መሆኑ ተገልጿል፡፡

ግብፅ ውስጥ የተከሰተውን ሕዝባዊ አመፅ ተከትሎ የሙባረክ መንግሥት ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢሳም ሻሪፍ የካቲት 24 ቀን 2003 ዓ.ም. በግብፅ ከፍተኛ ወታደራዊ ምክር ቤት ተሹመዋል፡፡ የ58 ዓመቱ ኢሳም እ.ኤ.አ. ከ2004 እስከ 2005 የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ አዲስ አበባ በመምጣት የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ወደ አዲስ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንደሚፈልጉ ቢገልጹም፣ የጉብኝታቸው ጊዜ መቼ እንደሚሆን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡፡

ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ 5,250 ሜጋ ዋት የሚያመነጨውን የታላቁ ሚሌኒየም ግድብን በይፋ ካስታወቀች በኋላ ግብፅ የተለያዩ የዲፕሎማሲ ጫናዎች ለመፍጠር እየጣረች የቆየች ቢሆንም፣ አሁን ከዓባይ ተፋሰስ አገሮች ጋር በውኃው ክፍፍል ላይ ለመደራደር እየተንቀሳቀሰች ነው፡፡ የግብፁ የውኃ ሀብት ሚኒስትር ሑሴን አል አትፋይ እንደገለጹት፣ ግብፅ ከላይኛው የተፋሰሱ አገሮች ጋር ያላትን የውኃ ክፍፍል ከግጭት ይልቅ በድርድር መፍታት ብቸኛው አማራጯ እየሆነ ነው፡

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Making a donation to Aend-Ethiopia radio station
ON AIR WUST 1120 AM Sunday 3PM - 4PM
Thank you for your donation.

Pulpit rock
Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

ESFNA 2010 SJ, CA
ESFNA
April 2011
S M T W T F S
« Mar   May »
 12
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930