EthioGreen LLC is a registered import / export company located in Washington, DC
202-558-8337
EthioGreen
President Obama Explains Healthcare

President Obama Explains Healthcare.gov
Ethiopian Political Parties
Ethiopian Political Parties
Categories

Ethiopian Television ETV Satellite Frequency
Struggle Over the Nile – Tension and suspicion

- ከ32.8 ቢሊዮን ብር በላይ አበድሯል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ69 ዓመት ታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን 4.2 ቢሊዮን ብር በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ማትረፉን ምንጮች ገለጹ፡፡ ይህ ከፍተኛ የተባለለት ትርፍ ከታክስ በፊት የተገኘ ሲሆን፣ የትርፉ መጠንም ባንኩ ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ወቅት ካገኘው ያልተጣራ ትርፍ ጋር ሲነፃፀር በ50 በመቶ እንደሚበልጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ለባንኩ ትርፋማነት አስተዋፅዖ ካደረጉት አገልግሎቶች መካከል ባንኩ የሰጠው የሐዋላ አገልግሎትና ለወጪ ንግድ ዘርፉ የሰጠው አገልግሎት ከፍ ያለ መሆኑ ተጠቃሽ መሆኑን፣ ስማቸውን ለመግለጽ ያልፈለጉ የባንኩ ባለሙያ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡በዚሁ በተገባደደው ዓመት ባንኩ ከሐዋላ አገልግሎት ከሦስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ሲያገኝ፣ በወጪ ንግድ ዘርፉ በኩል ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ማስገባት ችሏል፡፡በዚሁ በጀት ዓመት ተጠቃሽ ከሆኑት የባንኩ እንቅስቃሴዎች መካከል የቁጠባው ዘርፍ ከፍተኛ እመርታ ሲያስመዘግብ፣ በበጀት ዓመቱ ባንኩ 30 ቢሊዮን ብር ተቀማጭ ሒሳብ ማሳየት ችሏል፡፡ ይኼም በባንኩ ተቀማጭ ሒሳብ ያለውን ተቀማጭ ገንዘብ ወደ 86 ቢሊዮን ብር እንዳሳደገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ለባንኩ ተቀማጭ ሒሳብ ማደግ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ ባንኩ በዚሁ ዓመት የከፈታቸው 160 ቅርንጫፎች ዋነኛው መሆናቸውን የገለጹት የባንኩ ባለሙያ፣ በእነዚህ 160 ቅርንጫፎች ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ሒሳብ ተገኝቷል ብለዋል፡፡የባንኩ ተቀማጭ ሒሳብና ትርፍ ከተጠበቀው በላይ ማደጉን ለሪፖርተር የገለጹት የባንኩ ባለሙያ፣ ባንኩ በዚሁ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ32.8 ቢሊዮን ብር በላይ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ብድር መስጠቱን አስታውቀዋል፡፡የባንኩ እንቅስቃሴ በሚስተዋል መንገድ ማደጉን ያወሱት የባንኩ ባለሙያ፣ የባንኩ የተበላሸ ብድር መጠንም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ 0.84 በመቶ መውረዱን፣ ይኼም በአኀዝ ከ300 ሚሊዮን ብር በታች እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡
ከሰባት ዓመት በፊት የባንኩ የተበላሸ ብድር 50 በመቶ ደርሶ እንደነበረ የሚታወቅ ሲሆን፣ አንድ ባንክ በዓለም አቀፉ መመዘኛ ደረጃ ጤናማ እንዲባል የተበላሸ ብድሩ ከአምስት በመቶ በታች መሆን አለበት ከሚለው ደረጃ በጣም የወረደ ነበር፡፡
ባንኩ በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት የባንኩን ትርፍና የበጀት ዓመቱን እንቅስቃሴ፣ በሚኒስትር ማዕርግ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በሆኑት በአቶ በረከት ስምዖን ለሚመራው ለባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አቅርቦ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡

61 Responses to “የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን 4.2 ቢሊዮን ብር አተረፈ”

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Making a donation to Aend-Ethiopia radio station
ON AIR WUST 1120 AM Sunday 3PM - 4PM
Thank you for your donation.

Pulpit rock
Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

ESFNA 2010 SJ, CA
ESFNA
July 2011
S M T W T F S
« Jun   Aug »
 12
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31