EthioGreen LLC is a registered import / export company located in Washington, DC
202-558-8337
EthioGreen
President Obama Explains Healthcare

President Obama Explains Healthcare.gov
Ethiopian Political Parties
Ethiopian Political Parties
Categories

Ethiopian Television ETV Satellite Frequency
Struggle Over the Nile – Tension and suspicion

ድርቅ – ረሃብ ‹‹እንገደገና››
በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ፣ አልጄዚራ፣ ቢቢሲንና ኢሪንን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እያስተጋቡት ያለው ይኼው ኢትዮጵያን ማዕከል ያደረገውና በምሥራቅ አፍሪካ የተከሰተው ረሃብ ግን እጅግ አስጊ ነው፡፡ በየአምስት ዓመቱ ተመሳሳይ ድርቅና ረሃብ ሲያጋጥማት የሚስተዋለው ኢትዮጵያም፣ ዘንድሮም ምሥራቃዊ ክፍሏ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቱ ተዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም የአስቸኳይ ዕርዳታ ጥሪ አድርጓል፡፡
ባለፈው ዓመት አስቸኳይ ዕርዳታ ይፈልግ የነበረው የተራበ ሕዝብ 3.2 ሚሊዮን ሲሆን፣ ዘንድሮ በ1.3 ሚሊዮን ከፍ ብሎ 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ መራቡን መንግሥት ይፋ አድርጓል፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ ውስጥ ለረሃብ የተጋለጠውን ሕዝብ ቁጥር በተመለከተ በመንግሥትና በዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት መካከል ስምምነት አልነበረም፡፡ መንግሥት አምስት ሚሊዮን ሕዝብ ብቻ መራቡን ሲገልጽ፣ አይኤምኤፍና ኦክስፋም ኢንተርናሽናል በበኩላቸው ወደ አስራ አንድ ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ተርቧል የሚል መግለጫ ሰጥተው ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የተራበውን ሕዝብ ቁጥር አስመልክቶ ልዩነት የለም፡፡

ረሃብ ወይስ የምግብ እጥረት . . . ?
የኢትዮጵያ መንግሥትን ጨምሮ የተለያዩ መንግሥታት የተከሰተው ወቅታዊ ድርቅ ያስከተለው የምግብ እጦት በረሃብ ደረጃ ሊገለጽ አይገባም የሚል መከራከርያ ያቀርባሉ፡፡ ሌሎች ተንታኞችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግን ችግሩ በረሃብ ደረጃ ሊገለጽ የሚችል መሆኑን እየጠቆሙ ነው፡፡ የእንግሊዝኛው አቻ ቃል ‹‹Famine›› የሆነው ረሃብ በተለያዩ ወገኖች አንጻራዊ ልዩነት ባለው መንገድ ሲተረጐም ይስተዋላል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ከሁለት ዓመት በፊት በአገሪቱ ውስጥ በተከሰተው ድርቅ የተራበው ሕዝብ ቁጥር ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር ሲያጨቃጭቀው የተስተዋለ ሲሆን፣ ‹‹ረሃብ ነው አይደለም፤›› በሚልም ከተቃዋሚዎቹ ጋር ተወዛግቧል፡፡ ተቃዋሚዎች በወቅቱ የተከሰተው ችግር ከፍተኛ እንደሆነ በመግለጽና መንግሥት የተራበውን ሕዝብ ቁጥር ደብቋል በማለት የተከሰተው ቀውስ ‹‹በረሃብ›› ደረጃ የሚገለጽ ነው ሲሉ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ ሥልጣን ላይ በቆየበት ዘመን መቼም ቢሆን የረሃብተኞችን ቁጥር ደብቆ እንደማያውቅ፣ በየአምስት ዓመቱ የሚከሰተው ድርቅም የምግብ እጥረት ከማስከተሉ ውጪ ‹‹ረሃብ›› ሊሰኝ የሚችል መጥፎ ደረጃ ላይ አለመድረሱን ያስረዳል፡፡ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የረሃብተኞችን ቁጥር ከፍ የሚያደርጉት ዕርዳታ ሰጪዎችን ለማሳመን ቁጥሩን ከፍ ማድረግ ስለሚፈልጉ መሆኑን ጠቅላይ ማኒስትር መለስ ዜናዊ በፓርላማ አስረድተው ነበር፡፡ ‹‹አላርሚስትስ›› ሲሉም ትችት ሰንዝረውባቸው ነበር፡፡

ከድርቅ ወደ ድርቅ . . .
የአልጄዚራ ዘገባ እንደሚያመላክተው፣ በአካባቢው እንዲህ ዓይነት አደጋ የተከሰተው ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው፡፡ በተለይ ከሶማሊያ ወደ ኢትዮጵያና ኬንያ የሚጓዙ ረሃብተኞች በመንገድ ላይ ሕይወታቸውን እያጡ እንደሚገኙም ይኼው ዘገባ ያመለክታል፡፡
እ.ኤ.አ በ2009 በኢትዮጵያ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ተከስቶ በነበረው ረሃብ የተጠቃው ሕዝብ ቁጥር አሁን ከተራበው እጥፍ የነበረ ቢሆንም፣ የአሁኑ በደረጃው የከፋ እንደሆነ የዩኤንኤችሲአር (UNHCR) ኃላፊዎች ይናገራሉ፡፡
የተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ ኃላፊ አንቶንዮ ጉተርስ እንደሚሉት፣ በአካባቢው ያለው አደጋ እጅግ አስደንጋጭ ነው፡፡ በተለይ ሶማሊያን አስመልክተው ሲናገሩ፣ ‹‹በዘመናችን በሶማሊያ የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታ ገጥሟል፡፡ ወደ ካምፕ የሚገቡ በጣም የተጎሳቆሉና የተራቡ ሰዎች ሳይ ለመጀመርያ ጊዜዬ ነው፤›› ብለዋል፡፡ ሦስት ልጆቻቸው መንገድ ላይ የሞቱባቸውን አንዲት እናት ማየታቸውን በመግለጽ፡፡
በተለይ ደደአብ በተባለው በሶማሊያና በኢትዮጵያ ጠረፍና ኬንያ ውስጥ በሚገኘው ካምፕ ውስጥ የሚገቡ ረሃብተኞችን የተመለከተው የአልጄዚራ ዘጋቢ፣ ‹‹በእነዚህ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ የምትመለከተው ሰው ሞትን የሚጠብቅ ብቻ ነው፤›› ሲል የተመለከተውን አሳዛኝ ሁኔታ ገልጿል፡፡

One Response to “ኢትዮጵያም፣ ዘንድሮም ምሥራቃዊ ክፍሏ በከፍተኛ ድርቅ መጠቃቱ ተዘግቧል፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥትም የአስቸኳይ ዕርዳታ ጥሪ አድርጓል፡፡”

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Making a donation to Aend-Ethiopia radio station
ON AIR WUST 1120 AM Sunday 3PM - 4PM
Thank you for your donation.

Pulpit rock
Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

ESFNA 2010 SJ, CA
ESFNA
July 2011
S M T W T F S
« Jun   Aug »
 12
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31