EthioGreen LLC is a registered import / export company located in Washington, DC
202-558-8337
EthioGreen
President Obama Explains Healthcare

President Obama Explains Healthcare.gov
Ethiopian Political Parties
Ethiopian Political Parties
Categories

Ethiopian Television ETV Satellite Frequency
Struggle Over the Nile – Tension and suspicion

VOA Amharicሰሞኑን በተለያዩ ድረ-ገጾች፣ ብሎጎችና የሬድዮ ጣቢያዎች የቪኦኤን የውስጥ አሰራር አስመልክቶ የተነሱ አስተያየቶችንና ዘገባዎችን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ ምላሾችን በዝርዝር እንመልከት።የአፍሪካ ቀንድ ስራ አስኪያጅ ዲቪድ አርኖልድ ፤ ቪኦኤን የሚያስተዳድረው Broadcasting Board of Governors የኢትዮጵያን ጉብኝት ተከትሎ፤ ለአማርኛው ዝግጅት ክፍል በሰጡት አስተያየት ሁኔታው እስኪጣራ በእረፍት እንዲቆዩ ተደርገው፤ በአሁኑ ወቅት ወደ እንግሊዝኛው ክፍል ተዛውረዋል። ይኽ ለምን እንደሆነ ሬዲሽ ሲናገሩ፤“የዴቭድ አርሎንድ ጉዳይ ስለሚገኝበት ህኔታ መናገር አልፈልግም። ዴቪድ አርሎንድ በቪኦኤ ከፍ ያለ ስፍራ የሚሰጠው ነው። እንደ ዩናይትድ ስቴትስ ሰራተኛ መብቶች አሉት። በቀረበው ዜና ላይ ተፈጥሯል በተባለው የመረጃ መዛባትም ሆነ በተላለፈው ቃለ ምልልስ ውስጥ እርሱ ስለነበረው ሚና እየፈተሽን ነው። ፍተሻው እንዳለቀ ዴቪድ አርሎንድ ምን እንደሚሰራ እንወስናለን።”በአማርኛው ዝግጅት በድረ-ገጹ አስፍሮት የነበረው ዘገባ መነሳቱ፤ የመገናኛ ብዙሃን ነጻነትን ይጻረራል በሚል በርካታ ዘገባዎችና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።  “ቦርድ ኦቭ ገቨርናንስ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያደረጉትን ውይይት በተመለከተ የወጣ ዜና ነበረ። ዜናው ከወጣ በኋላ እንዲነሳ ተደርጓል።  ሌላኛው የውይይት ርእስ፤ የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ከሁለት ሳምንት በፊት የተካሄደ ህዝባዊ ስብሰባን ጋዜጠኛ ልኮ ዘግቦ አየር ላይ እንዳይውል ተከልክሏል የሚል ነው። የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የአፍሪካ ክፍል ሃላፊ ጉዌን ዲላርድ ይሄ መረጃ የተሳሳተ ነው ይላሉ። የአሜሪካ ድምጽ መጀመሪያውኑም ጋዜጠኛ አላከም ይላሉ።የኢትዮጵያ መንግስት የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ለተቃዋሚዎች ያደላል፤ በሃገር ውስጥ መንግስት የሚሰራቸውን የመሰረተ ልማት ግንባታዎች፣ የአገር ገጽታዎችና የአስተዳድር እመርታዎች ዋጋ ይነሳል ሲል ይከሳል።የኢትዮጵያ መንግስት 42 ገጽ ያለው የክስ መዝገብ ለአሜሪካ ኢምባሲና ለቪኦኤ አስገብቷል። ባለፉት ጥቂት ወራት የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ስርጭቶች ላይ መንግስቱ ያልወደዳቸውንና ሚዛናዊ ያልሆኑ ያላቸውን ዘገባዎች አትቷል።በዚህ ላይ የቪኦኤ አስተዳደር ጉዳዩን በገለልተኛ አካላት እያስጠና መሆኑን ስቲብ ሬዲሽ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት በደፈናው ቪኦኤ የተሟሉ ዘገባዎችን አያቀርብም ከማለት ይልቅ ዝርዝር ክስ ማቅረቡ፤ የተሻለ አሰራር መሆኑ የጠቆሙት ሬዲሽ፤ ለዚህም ቪኦኤ በገለልተኛ አካላት የተጠና ምላሽ ይሰጣል ብለዋል።

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Making a donation to Aend-Ethiopia radio station
ON AIR WUST 1120 AM Sunday 3PM - 4PM
Thank you for your donation.

Pulpit rock
Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

ESFNA 2010 SJ, CA
ESFNA
July 2011
S M T W T F S
« Jun   Aug »
 12
3456789
10111213141516
17181920212223
24252627282930
31