EthioGreen LLC is a registered import / export company located in Washington, DC
202-558-8337
EthioGreen
President Obama Explains Healthcare

President Obama Explains Healthcare.gov
Ethiopian Political Parties
Ethiopian Political Parties
Categories

Ethiopian Television ETV Satellite Frequency
Struggle Over the Nile – Tension and suspicion

politically Offensive, economically defensiveበቅርቡ ከሽብርተኝነት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሰዎችን በተመለከተ

ነገሩ በፍርድ ቤት እየታየ ነው፡፡ በፍርድ ቤት እየታየ ያለን ጉዳይ የሚዘግቡ ጋዜጦች ክሱ ምን እንደሆነ ሳያዩ፣ ማስረጃዎችን ሳይመለከቱ ተጠርጣሪዎቹ ነፃ ናቸው የሚሉት የፍርድ ሒደቱ በፍጥነት ባለመከናወኑ ሳይሆን፣ የጋዜጠኝነት ሀሁ የማይገባቸው ወይም እንዲገባቸው የማይፈልጉ ጋጠ ወጦች በመሆናቸው ነው፡፡ የጋዜጠኛ የመጀመሪያ ሥነ ምግባር የሁለቱን አስተያየት መስማት ነው፡፡ ነገሮችን በጥሞና ማጥናት ነው፡፡ ማስረጃዎችን መፈተሽ ነው፡፡ ይህን ሳያደርጉ ዘሎ አለመጻፍ አለመናገር ነው፡፡ የጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር የሚጠይቀው ይኼን ነው፡፡ ይኼን ሥነ ምግባር አልፈው የሚንጣጡ ጋዜጠኞች ካሉ ችግሩ የራሳቸው እንጂ ለፍርድ ቤት በማቅረብ ላይ መዘግየት ስለታየ አይደለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት በአገራችን የሚካሄደው የሽብር እንቅስቃሴ ሦስት ዋና ዋና ተዋናዮች አሉት፡፡ አንደኛውና ዋናው የኤርትራ መንግሥት ነው፡፡ የእዚህን ቡድን አቋም ሕዝቡ ያውቀዋል፡፡ ሻዕቢያ የአቋም ለውጥ አላሳየም፡፡ አካባቢውን የማተራመስ ስትራቴጂ ይዞ ነው እየሠራ ያለው፡፡ ሁለተኞቹ ሻዕቢያ በቀጥታ የሚያሰማራቸው ነጭ ለባሾች ናቸው፡፡ እነዚህ አልሻባብን ይመለከታሉ፡፡ ኦነግን፣ ኦብነግንና ግንቦት 7 ብሎ የሰየመውን ቡድን ይመለከታሉ፡፡ እነዚህ ቡድኖች በዚህ ፓርላማ አሸባሪ ተብለው ተፈርጀዋል፡፡ ዋና ቢሮአቸውም አስመራ ነው፡፡ የሚንቀሳቀሱትም አስመራ በተቀየሰው ስትራቴጂ መሠረት ነው፡፡ እነዚህ በጣም የታወቁ ተዋንያን ናቸው፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ በሰላማዊ መንገድ እንሠራለን ብለው ያወጁ ናቸው፡፡ አንዳንድ የመድረክ መሪዎች ከእነዚህ የሻዕቢያ ነጭ ለባሾች ጋር በመተባበር በሕጋዊ ፓርቲ ሽፋን የነኦብነግ፣ የነኦነግና የግንቦት 7 አስፈጻሚ ሆነው እየሠሩ ነው፡፡ አሁን የታሰሩ ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህ የታሠሩት ሰዎች የአሸባሪ ድርጅት አባላት መሆናቸውን የሚያሳይ አሳማኝ ማስረጃ አለን፡፡ ማን የማን ድርጅት አባል መሆኑን እያወቅን ያላሰርናቸው ሰዎች አሉ፡፡ እነዚህን ግለሰቦች ያላሰርንበት ምክንያቱ ሁለት ነው፡፡ የመጀመሪያው ሰዶ ማሳደድ አያስፈልግም በሚል ነው፡፡ በፍርድ ቤት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ስላላገኘንባቸው ዝም ያልናቸው አሉ፡፡ እስካሁን ለታሰሩት ግን የአሸባሪ አባል ስለመሆናቸው አሳማኝ ማስረጃ አለን፡፡

Leave a Reply

You must be logged in to post a comment.

Making a donation to Aend-Ethiopia radio station
ON AIR WUST 1120 AM Sunday 3PM - 4PM
Thank you for your donation.

Pulpit rock
Aend-Ethiopia Radio Address (Ethiopian 4th General Election 2010)

ESFNA 2010 SJ, CA
ESFNA
October 2011
S M T W T F S
« Sep   Nov »
 1
2345678
9101112131415
16171819202122
23242526272829
3031