Here is the Music Player. You need to installl flash player to show this cool thing!
Long time St. George FC and Ethiopian National Team legend Engdawork Tariku (Sebeta) passed away last weekend in the DC area after long battle with cancer and other health issues. Sebeta was well known in the soccer community as well as ESFNA Guest of Honor in 2003. .

ቋሚ የሆነ የመተማመንና እጅ ለእጅ ተይይዞ አገርን በጋራ የማሳደግ አመለካከት መያዝ አልቻልንም፡፡ ጠላት ወረረን ሲባል እንሰባሰባለን፡፡ችግሩ ሲያልፍ ግን እንራራቃለን፡፡ የዓባይ ግድብ ሲባል እጅ ለእጅ እንያያዛለን፡፡ የቫት፣ የሊዝና የመሬት ጉዳይ ሲነሣ ግን በዓይነ ቁራኛ እንተያያለን፡፡እንደዚህ ዓይነቱ ገጽታ አስቸጋሪ የዓለም ሁኔታ ባለበት ወቅት ይቅርና በተደላደለ ሁኔታ ውስጥ ብንገኝም መናቆሩ አያዋጣም፡፡ መጠራጠሩ አያራምድም፡፡ አሁን ያለንበት የዓለም ሁኔታ ደግሞ አስቸጋሪ ነው፡፡ የአውሮፓውም፣ የአሜሪካውም ኢኮኖሚ እየተልፈሰፈሰ ነው፡፡ ከአዘቅት ውስጥም እየገባ ነው፡፡ የኢኮኖሚ ችግሩም ቀስ በቀስ የፖለቲካ ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ልዩ ብስለትና ልዩ አካሔድ ይጠበቅብናል፡፡ ከሁሉም በፊት ግን አላስፈላጊ የውስጥ ችግርን አለመፍጠር ነው፡፡ እንደ ሕዝብ አንድነታችንን አጠንክረንና የላቀ ራዕይ ይዘን በላቀ ጥረት የምናድግበትን አመለካከት ልንይዝ ይገባል፡፡ የውስጥ አቅማችንን፣ አንድነታችንን፣ እምነታችንን፣ ትስስራችንን የሚያላላ ሁሉ ማስወገድ ይኖርብናል፡፡ ሕዝብ ለሕዝብ ብቻ ሳይሆን ባለሀብቱም፣ ባለሙያውም፣ ባለሥልጣኑም፣ ወጣቱም ሁሉም በጋራ ለአገር ደኅንነትና ዕድገት፣ ጥንካሬና ሰላም፣ መረጋጋትም ማሰብና መሥራት ይኖርበታል፡፡ አስተማማኝና ዘላቂ ዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሥርዓትንም እውን ለማድረግ መረባረብ ይገባናል፡፡
EthioGreen

